እንኳን ወደ አዲስ አበባ ደንብ ማስከበር የቅሬታ መሙያ ሲስተም በድህና መጡ!!
ስለ አቤቱታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ
ሰላም ጤና ይስጥልኝ! ይህ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የባለጉዳይ የቅሬታ ማቅረቢያ ፎርም ሲሆን ባለጉዳይ/ተገልጋይ/ በተገለገለው አገልግሎት ካልተደሰተ/ቅሬታ ከተሰማው ይህንን ቅፅ በጥንቃቄ በመሙላት ለሚመለከተው ክፍል ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል። አገልግሎታችንን ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን።
- ማንኛውም የደንብ መተላለፍ ፈጽሞ የቅጣት ክፍያ የተጣለበት፣ ንብረቱ የተወረሰበት፣ የታሸገበት ሰው ቅጣቱን ከከፈለበት ቀን አንስቶ በሶስት የሥራ ቀናት ውስጥ ጥፋቱ በተፈጸመበት ወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት መቀጮውን የከፈለበትን ደረሰኝ በመያዝ አቤቱታውን በፅሑፍ ሊያቀርብ ይችላል፣
- አቤቱታ የቀረበለት የወረዳ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ላፊ የቀረበለትን አቤቱታ አግባብነትካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብና በመመርመር በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለአቤቱታ አቅራቢው በፁሁፍ ምላሽ ይሰጣል፣
- በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ (1) በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ቅሬታ አቀራቢ ውሳኔው በተሰጠው በአሥር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ለክፍለ ከተማዉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት በፅሁፍ ሊያቀርብ ይችላል፣
- አቤቱታ የቀረበለት የክፍለ ከተማዉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ሀላፊ የቀረበለትን አቤቱታ አግባብነት ካላቸው ሕጎች ጋር በማገናዘብና በመመርመር በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ለአቤቱታ አቅራቢው በጽሑፍ ምላሽ ይሰጣል፤ በተሰጠው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ቅሬታዉን በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ለማዕከሉ ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት ሀላፊ ማቅረብ ይችላል፣
አድራሻ
አዲስ አበባ ደንብ ማስከብር ማስደበር አድራሻ